ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሚሚ አለማየሁ የትዊተር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆና መመረጧን ድርጀቱ አስታውቋል፡፡
እያደገ በመጣው ገበያ ከ20 ዓመታት በላይ የኢንቨስትመንት እና የገበያ ባለሞያነት ልምድ ያላት ሚሚ ለቦርድ አባልነት አብቅቷታል ተብሏል፡፡
ሚሚን ለቦርድ አባልነት ያበቃት በተለያዩ አዳጊ ገበያዎች በመንግሥት እና የግል የኢንቬስትመንት እና የፋይናንስ ዘርፎች ከ20 ዓመታት በላይ በመስራት ያካበተችው ልምድ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ሚሚ ያላት ይህ ሰፊ ተሳትፎ እና ልምድ ትዊተር በዓለም ዙሪያ የህዝብ ውይይትን ለማዳበር የያዘውን ተልዕኮ ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የትዊተር ገለልተኛ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ ፒቼት ገልፀዋል፡፡
ሚሚ የትዊተርን ማህበራዊ ኃላፊነት እና ዓለምአቀፋዊ ማህበረሰብን የመፍጠር ተልዕኮ ትጋራለች ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው ትዊተር በተለይ በአፍሪካ ያለውን ተልዕኮ ለማስፋፋት በጋና ቢሮ በመክፈቱ የሚሚን ስራ እንፈልገዋለን ብለዋል፡፡
በዓለም ላይ ህዝባዊ ውይይቶች እንዲዳብሩ ዓልሞ እየሰራ ያለውን ትዊተር አደንቃለሁ ያለችው ሚሚ በበኩሏ የትዊተር ገለልተኛ ቦርድ አባል በመሆኔ ኩራት ተሰምቶኛል ስትል ደስታዋን ገልፃለች፡፡ ሚሚ አለማየሁ በማስተርካርድ የመንግስት እና የግል ጥምረት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያለገለች ትገኛለች፡፡
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች